cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

TIKVAH-MAGAZINE

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

Show more
Advertising posts
196 505
Subscribers
-3124 hours
-177 days
+5930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ጥቆማ "በጎ ስጦታ" የበጎ አድራጎት ድርጅት የተባለ አገር በቀል ድርጅት ከውጪ ካሉ ለጋሽ አካላት ጋር በመተባበር በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ያላቸው ግን በአቅም ማነስ ምክንያት ትምህርታቸውን ለመከታተለ የከበዳቸውን ተማሪዎች ድጋፍ ለማረግ ማቀዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ተቋሙ አሁን ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በኪያሜድ ኮሌጅ በነርሲንግ ዲፓርትመንት በዲፕሎማ መርሀ ግብር 20 ሴት ተማሪዎችን ተቀብሎ ከትምህርት ጋር የተያያዙ ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እድሉን ማመቻቸቱን ገልጿል። የዚህ እድል ተሳታፊ የሆኑ ልጆች ምን ማሟላት አለባቸው? - ከ 2014 እስከ 2015 የ 12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ለዲፕሎማ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያመጡ፤ - በዲፕሎማ በቀን መርሀ ግብር ነርሲንግ መማር ፍላጎት ያላቸው። - አቅም እንደ ሌላቸው ከቀበሌ ማስመስከር የሚችሉ፤ - ትምህርቱን ከጀመሩ በኋላ ውጤታቸውን አስጠብቀው መጓዝ የሚችሉ፤ - ተቋሙ ከትምህርት ውጪ ያሉ ወጪዎችን ስለማይሸፍን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ይህንን የምታሟሉ / በአከባቢያችሁ በትምህርታቸው ጎበዝ የሆኑ የምታቋቸው ካሉ በዚህ እድል እንዲጠቀሙ ይህንን መልዕክት አድርሷቸው። ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም @elzabet18/@Dr_Daniel_D ወይም በስልክ ቁጥር +251912671410 /+251938327771/ +251953146834 ላይ ያግኙ። BegoSitota.com #TikvahEthiopia
Show all...
👏 33 13😢 6😡 4
በወጣት ቃልኪዳን ባህሩ ዙሪያ የወጡ መረጃዎች እንዲጣሩ ተጠየቀ በወጣት ቃልኪዳን ባህሩ ላይ በተፈጸመው አስገድዶ መድፈር፣ ዕገታና ጥቃት ዙሪያ የወጡ መረጃዎች እንዲጣሩ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበርና 4 አጋር ድርጅቶች ጠይቀዋል። ወጣት ቃልኪዳን ባህሩን በተመለከተ በማኅበራዊ ሚዲያዎች መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በፌስቡክ ገጹ ላይ "አንዲት ወጣት እንደተደፈረች ተደርጎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው" ሲል ግንቦት 10 ቀን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል። ፖሊስ በመግለጫው ምን አለ? - ወጣቷ ሚያዚያ 16 ቀን 2016 ዓ/ም ወጣቷ  በግለሰቦች ከቤት ተወስጄ ተደፈርኩ በማለት ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመልክታለች፤ - ፖሊስ በወቅቱ በፍጥነት በዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል ምርመራ እንድታገኝ ቢያደርግም ውጤቱ  ምንም አይነት ፆታዊ መደፈር እንዳልደረሰባት የሚያሳይ ነው፤ - ወጣቷ ከዚህ ቀደምም በ2014 ዓ/ም ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሞብኛል ብላ አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመልክታ የነበር ቢሆንም የተደረገው የጤና ምርመራ ምንም አይነት ፆታዊ መደፈር  እንዳልደረሰባት ያሳያል፤ - ወጣቷ ሳትደፈር ተደፈርኩ በማለት ሀሰተኛ ክስ ከማስዝገብ ባሻገር ጉዳዩን በማህበራዊ ሚዲያ እንዲናፈስ ማድረጓ የህግ ተጠያቂነት የሚያከትል ድርጊት ነው ሲል ጠቅሷል። ማኅበሩ ይህ መረጃ እንደደረሰው ቃልኪዳንን ጠርቶ ከቤተሰቦቿ ጋር ስለጉዳዩ ማውራቱንና በቅድሚያ ከቤተሰቦቿ ጋር ካሉበት የሸራ ቤት ጊዜያዊ መጠለያ እንዲመቻችላቸው ቅድሚያ ሰጥቶ መስራቱን ገልጿል። የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በመግለጫቸው ምን አለ ? - የቴሌግራም መልዕክቶችን እንዲሁም ለተጠቂ እናት በስልክ ሲደርሳቸው የነበረው ዛቻና ማስፈራሪያ አስመልክቶ ፖሊስ በምን መንገድ አስፈላጊውን ምርመራ እንዳደረገ ከምርመራው ያገኘውን ውጤት በግልፅ እንዲያሳውቀን፤ - ይህ አይነት የተወሳሰበ ወንጀል በቴክኖሎጂ፣ በፎረንሲክ እንዲሁም በልዩ ልዩ የፕሮፌሽናል ማስረጃ በማረጋገጥ የሚፈታ ወንጀል በመሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ይህን አድርጎ ከሆነም ውጤቱን በግልፅ እንዲያሳውቀን፤ - የሚኒሊክና የጴጥሮስ ሆስፒታሎች የህክምና ማስረጃውን የምርመራውን ሂደት በግልፅ የሚያሳይ ውጤት እንዲገለፅልን ሲል ጠይቋል። ለተባባሪ አካላት ባቀረበው ጥሪም "ስለተጠቂ ቃልኪዳን ባህሩ እየተሰራጨ ያለውን መረጃ ትክክለኛነት በማጣራትና በነበሩ ሂደቶች ዙሪያ የተደረገላት የህክምና ሂደቶች ትክክለኛነት ተጣርቶ ፍትህ እስክታገኝ ድረስ ከተቋማችን ጋር ተባብረው እንዲሰሩ" ሲሉ አንስተዋል።
Show all...
👏 82🤔 13😡 5 4😨 2
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ ባለፉት 26 ቀናት 1.8 ሚሊዮን ሰዎች በወባ ተይዘው 314 ሰዎች መሞታቸውን ሪፖርት አመለከተ በኢትዮጵያ ባለፉት 26 ቀናት ከ1.8 ሚሊዮን ሰዎች በወባ ተይዘው 314 ሰዎች መሞታቸው የጤና ክላስተር ሪፖርት አመለከተ። ሪፖርቱ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች 35 በመቶ የሚሆኑት በኢሮሚያ ክልል የተመዘገቡ መሆኑ ሲጠቆም በክልሉ የወለጋ አካባቢ ከፍተኛ የወባ ስርጭት እንዳለ ተጠቁሟል። በበሽታው ከተያዙ ሰዎጭ 22 በመቶ የሚሆኑት በአማራ፣ 13 በመቶ በደቡብ ምዕራብ እንዲሁም 10 በመቶ በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ መሆናቸውን ተመላክቷል። በሀገሪቱ  በወባ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ባለፈው ወር ከነበረበት በ29 በመቶ የጨመረ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ በ27 በመቶ መጨመሩ በሪፖርቱ ተመላክቷል። #MalariaReport
Show all...
😢 12
01:00
Video unavailableShow in Telegram
Last and final day tomorrow to visit Big 5 Construct Ethiopia at Millennium Hall, Addis Ababa. The show was officially opened in the presence of H.E. Temesgen Tiruneh, Deputy Prime Minister of Ethiopia and H.E. Chaltu Sani, Minister, Ministry of Urban and Infrastructure. Big 5 Construct Ethiopia witnessed networks being built, collaboration being fostered and knowledge being exchanged. Check out the highlights. Register for free now: https://bit.ly/3UsrL5I Show opens tomorrow at 10:00AM. Come visit 150+ local and international exhibitors and attend 20+ industry workshops.
Show all...
1😡 1
00:59
Video unavailableShow in Telegram
ታላቅ የዋጋ ቅናሽ ከአያት ሪል ኢስቴት!!! 👌በኢትዮጵያ የመጀመሪያውና እጅግ  ግዙፉ በውስጡ ከ4000 በላይ ሱቆችን በያዘው በአያት የገበያ ማዕከል የንግድ ሱቆችን ለአጭር ጊዜ ብቻ ከሚቆይ ከከፍተኛ ቅናሽ  ጋር ለሽያጭ አቅርበናል። ➡️ከ30 ካሬ ጀምሮ የሚፈልጉትን የካሬ መጠን ዛሬውኑ በኢትዮጵያ ብር ብቻ ይገበያዩ! እንዳያመልጥዎ!!! ✅ ሲኤምሲ ሚካኤል ጀርባ በተንጣለለው የአያት መኖሪያ መንደር ውስጥ   ✅ በኢትዮጵያ ትልቁ የገበያ ማዕከል ጂምናዚየም፣ ሱፐርማርኬቶች፣ ፋርማሲዎች፣ ክሊኒኮች፣ ሲኒማ፣ ሬስቶራንቶች፣ የውበት ሳሎኖች፣ ቡቲኮች፣ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ባንኮች፣ Spa የመሳሰሉትን ሁሉንም ያካተተ የገበያ ማዕከል መኖርያ ቤት ከ ባለ ሁለት መኝታ ጀምሮ እስከ ባለ 3 መኝታ ድረስ በተለያየ የካሬ አማራጭ በ 15% ቅድመ ክፍያ ለአጭር ጊዜ ብቻ ከሚቆይ ከፍተኛ ቅናሽ ጋር በመሸጥ ላይ ነን።  ብድር ለምትፈልጉ ደምበኞቻችን 60% በ 3 አመት ከፍላችሁ ቀሪ 40% በ 9.5% ዝቅተኛ ወለድ እስከ 30 ዓመት በሚደርስ የረጅም ግዜ ክፍያ አማራጭ አዘጋጅተናል። ለመመዝገብ  የአያት ቤቶች የሽያጭ ከፍተኛ ኦፊሰርን ያግኙ +251911141372/251910531565 Telegram: https://t.me/Tese_Apartment
Show all...
2
አንድ እህቴን አፋልጉኝ ! " እህቴ ዮርዳኖስ ተሰማ ትባላለች። ያለችኝ አንድ እህቴ ናት። እድሜዋ ገና 14 አመት ነው። ግንቦት 8 /2016 ሐሙስ አመሻሽ 12:00 አካባቢ ከአ/አ ኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ አባጃሌ ከተሰኘ ሰፈር እደወጣች አልተመለሰችም። በእለቱ ከላይ ጥቁር እጅጌ ጉርድ ቲሸርት ከፊለፊቱ ቡራቡሬ ስዕል ያለው እና ከታች ቡና ወይ ሽሮ ከለር መሳይ ስስ ቀሚስ ለብሳ ነበር። ቤተሰቦቻችን ያሳደጉን በመከራና በእንግልት ነው እናታችን በጣም እየተጎዳች ነው አትቀመጥም በየቀኑ አገኛታለው ብላ አገር ለሐገር እየዞረች ነው። እህታችንን ያያት ወይም ያገኛት ከታች በተጠቀሱስ ስልክ ቁጥሮች ቢያሳውቁን ስንል በትህትና እንጠይቃለን። ስልክ ፦  0934490756 0925776169  0923150119  0970222977 " @tikvahethmagazine
Show all...
😢 138 10🤔 8🕊 6😨 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ናኦድ የሺጥላ " ሰው ላግኝ " ብሎ ከቤት እንደወጣ 5 ቀን ሆኖታል። እባካችሁን በምስሉ ላይ የሚታየውን ልጅ ያየ ወይንም ያለበትን የሚያውቅ ሰው ካለ በስልክ ቁጥሮች 0955 065 269፣ 0912 119 132፣ ወይም 0911 360 960 በመደወል እንድታሳውቁን ሲሉ ቤተሰቦቹ ተማጽነዋል። @tikvahethmagazine
Show all...
😢 73 3🤔 3🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
በሰሜን ሸዋ ዞን 8 ሺህ 73 ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ በሰሜን ሸዋ ዞን ባለፉት ወራት 72 ሺህ 455 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ 8 ሺህ 73 ሰዎች በወባ በሽታ የተጠቁ መኾናቸውን የዞኑን የጤና መምሪያ ዋቢ አድርጎ አሚኮ ዘግቧል። የወባ በሽታ በተጠቁ ሰዎች አቅራቢያ በተደረገ ተጨማሪ ምርመራ ደግሞ 159 ሕሙማንን መለየት መቻሉም ተነግሯል። የመምሪያው ኀላፊ ጸዳለ ሰሙንጉሥ በ2016 በጀት ዓመት የወባ ስርጭት ምጣኔ ወደ 5 በመቶ ዝቅ እንዲል ይጠበቅ እንደነበር ሲገልፁ ይሁን እንጂ አሁን ላይ በዞኑ የስርጭት መጠኑ 11 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ በተለይ በሸዋሮቢት፣ መርሃቤቴ፣ እንሳሮ፣ ምንጃር እና መሰል ቆላማ የዞኑ አካባቢዎች የበሽታው ስርጭት #ከፍተኛ እንደሆነ ጠቁመዋል። በማኅበረሰቡ ዘንድ የወባ በሽታ የሌለ እስኪመስል ድረስ መዘናጋት መኖሩን መምሪያ ኀላፊዋ ገልፀዋል። በጤና ተቋማት የሕክምና ግብዓት እጥረት መኖር እና ወቅታዊ የሰላም መደፍረስ ችግሮችም የወባ በሽታ የመከላከል ሥራ ለመሥራት እክል መሆናቸውን ለስርጭቱ መጨመር በምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡
Show all...
😢 27 7
Photo unavailableShow in Telegram
" በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ባለ ግጭት ምክንያት ዜጎች የጤና አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም - " የአለማቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የአለማቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭት እና ሁከት ምክንያት በተለይም በገጠር እና ራቅ ባሉ አካባቢዎች ህብረተሰቡ የጤና አገልግሎትን ማግኘት አለመቻሉን አስታውቋል። ኮሚቴው የቆሰሉ፣ የታመሙ፣ እርጉዝ ሴቶች፣ ህጻናት እና አካል ጉዳተኞች ተጠቂ እንደሆኑ ሲገልፅ በአማራ ክልል ያለው ግጭት የጤና አጠባበቅ አቅርቦትን በማስተጓጎል የመድሃኒት እና የህክምና ቁሳቁሶችን ለማቅረብ የሚደረገው ጥርት አዳጋች አድርጎታል ሲል ገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ አሁንም ያልተረጋጋ እንደሆነ፤ በትግራይ ክልል የተደረገው ግጭት የረዥም ጊዜ ጠባሳ እያሳረፈ እንደሆነና ይህም አሁንም የህዝቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት እየጎዳ እንደሆነ ኮሚቴው አመልክቷል።
Show all...
😢 17 4😡 4
#WIPO በኢትዮጵያ በዘረመልና ተያያዥ ባህላዊ እውቀቶች ላይ የፈጠራ ስራ ያበረከቱ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት መብት ማግኘት ሊጀምሩ መሆኑ ተገልጿል። የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) አባል ሀገራት እ.ኤ.አ ከሜይ 13-24 በጀኔቭ ባካሄዱት ዲፕሎማቲክ ኮንፍረንስ በአእምሯዊ ንብረት ፣ በዘረመል (Genetic) ሀብቶች እና በተዛማጅ ባህላዊ እውቀት መብት ጥበቃ ላይ የተመሰረተ አዲስ ዓለምአቀፍ ስምምነትን በተባበረ ድምፅ አጽድቀዋል፡፡ ኢትዮጵያም በድርድር ሂደቶቹ ከመሳተፍ ባሻገር ካላት ሰፊ የዘረመል ሃብቷ እና ባህላዊ እውቀቷ ተጠቃሚ እንድትሆን የሚያስችላትን አቋም በመያዝ የስምምነት ሰነዱን ፈርማለች። ይህ ስምምነት በጄኔቲክ ሃብት እና በተዛማጅ ማኅበረሰባዊ እውቀት ላይ ተመስርተው ለሚቀርቡ የፓተንት ማመልከቻዎች አመልካቾቹ የፈጠራዎቻቸውን የዘረመል ሀብቶች እና ተዛማጅ ማኅበረሰባዊ እውቀቶች መገኛ ምንጭ እንዲገልጹ ያስገድዳል ተብሏል። በተጨማሪም የፓተንት ሥርዓቱን ውጤታማነት ፣ ግልጽነት እና ጥራትን ለማሳደግ እንደሚረዳና በዘረመል ሀብቶች እና ተያያዥ ባህላዊ እውቀት ላይ አዲስነት ወይም ፈጠራዊ ብቃት የሌላቸው ፈጠራዎች ያለአግባብ ዕውቅና እንዳያገኙ ለመከላከልም እንሚያስችል ተጠቁሟል። (📹 በWIPO የተዘጋጀውን አጭር የመግጫ ቪዲዮ ይመልከቱ)
Show all...
30🤔 9😡 4😨 1